
የቦሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
ፈጣን እና ግልጽ የህዝብ አገልግሎት ለከተማችን ነዋሪዎች
ቅሬታዎን ያቅርቡ፣ ሂደቱን ይከታተሉ፣ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊ — መልዕክት ከአቶ ቸሩ ጌታቸው
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከማዕከል እስከ ወረዳ በአዋጅ ቁጥር 37/2005 እና በደንብ ቁጥር /2005 በድጋሚ ከተቋቋመ 2005 ዓ.ም በኋላ ተቋሙ አረጃግሮቱን በሰው ሃይል በግብዓቶች እና በአሰራር ከግዜ ወደ ግዜ እያሳደገ የመጣ ሲሁን እንዲያስፈፅም በአዋጅ በሃላፊነት የተሰጡትን በከተማው ውስጥ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶችን ስርዓት በማስያዝ በኩልም ከፍተኛ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ የሚገኝ ተቋም ነው። ከዚህ አንጻር የቦሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱም በተመሳሳይ ለተቋሙ በአዋጅ ደንብ መመሪያ እንዲተገበር በተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት መሰረት በክፍለ ከተማችን በሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች ላይ የሚያደርገውን የመከላከል መቆጣጠር እና እርምጃ አወሳሰድ ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ አጠናክሮ በመቀጠል የደንብ መተላለፍ ድርጊቶችን ስርዓት በማስያዝ በኩል ውጤታም ስራ ተሰርቷል። ለማሳያ ያክልም ከዓመታት በፊት በክፍለ ከተማችን በመሬት ወረራ እና ማስፋፋት በስፋት ይስተዋሉ የነበረው የደንብ ጥሰት አሁን ላይ በቅድመ መከላከል ስራ መቆጣጠር የተቻለበት ሁኔታ ሲኖር ከህገወጥ የጎዳና ላይ ንግድ አንጻር በመገናኛ ቦሌ ብራስ ጉርድ ሾላ እና ጎሮ አካባቢዎች በወንጀልና የትራፊክ አደጋ መንስኤ በሆነ አኳኋን በስፋት ይስተዋል የነበረውን ችግር መቅረፍና ስርዓት ማስያዝ የተቻለበትን የአሰራር አቅም መፍጠር የተቻለ ሲሆን ሌሎች የደንብ ጥሰቶችን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ስርዓት የማስያዝ ስራ በመስራት ላይ የምንገኝ ሲሆን በየ ዓመቱ እንደ ጽ/ቤትና በሁሉም ወረዳ የደንብ ጥሰትን በመከላከል መቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ በተሰራው የተቀናጀ ጠንካራ ስራ የደንብ ጥሰት ምጣኔን በዓመቱ በ25% ለመቀነስ የተያዘውን እቅድ በከፍተኛ ሁኔታ በማሻሻል ከ50% በላይ በመቀነስ ውጤታማ ስራ በመስራት ላይ እንገኛለን። ለዚህም የጽ/ቤታችንን ባለሞያዎች በጽ/ቤታችን ስር ያሉ የወረዳ አመራሮችና አጠቃላይ ባለሙያዎች የባለስልጣን መ/ቤቱ የበላይ አመራሮች እና ዳይሬክተሮች የክፍለ ከተማችን አስተባባሪ አመራሮች ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የክፍለ ከተማችን ነዋሪ ህብረተሰብ እያደረገልን ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እዲቀጥልና እስካሁን ለነበረው ከፍተኛ እገዛ በዚህ አጋጣሜ በራሴና በጽ/ቤቱ ስም ምስጋናዬን በአክብሮት እያቀረብኩ በቀጣይም ክፍተቶችን በማረምና ጥንካሬዎቻችንን አጠናክሮ ለማስቀጠል ጽ/ቤታችን በሚያደርገው ጥረት ድጋፋችሁ እንዳይለየን መልዕክቴን አስተላልፋለሁ። የደንብ ጥሰትን በጋራ እንከላከላለን!!!
— አቶ ቸሩ ጌታቸው፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ
- በስራ ቀናት ውስጥ በ48 ሰዓት ምላሽ እናገኛለን
- የቅሬታዎን ሂደት በቀላሉ ይከታተሉ
- ለክትትል የሚያገለግል ልዩ መለያ ቁጥር ያገኛሉ
እንዴት በተሻለ እናገለግልዎታለን
ተልዕኮ
በህብረተሰቡ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ የደንብ መተላለፎችና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራትን በመከታተልና በመቆጣጠር አዲስ አበባ ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ማራኪና ሰላማዊ እንድትሆን ማድረግ፡፡
ራዕይ
በ2022 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ለነዋሪዎቿ ምቹ እንዲሁም ለአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት ሆና ማየት፡፡
እሴቶች
- ተጠያቂነት
- ግልጽነት
- ለለውጥ ዝግጁነት
- የላቀ አገልግሎት መስጠት
- በእውቀት እና በዕምነት መስራትና መምራት
ለእርስዎ በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል የተዘጋጀ፦ ቀላል የቅሬታ አቀራረብ፣ ግልጽ ተጠያቂነት እና ፈጣን ምላሽ ለሁሉም ነዋሪዎች።
ሦስት ቀላል ደረጃዎች
- 1
ምን እንደተፈጠረ ይንገሩን
ወረዳዎን ይምረጡ፣ የጥሰቱን አይነት ይወስኑ እና ቦታውን በግልጽ ያስገቡ። ስልክዎን ማስገባትዎ ፈጣን መፍትሄ ለመስጠት ይረዳናል።
- 2
ያስገቡ እና መለያዎን ያስቀምጡ
ቅሬታዎን ይላኩ እና ልዩ የክትትል መለያዎን ያስቀምጡ። ይህን መለያ ተጠቅመው ሂደቱን መከታተል ይችላሉ።
- 3
ጥያቄዎን ይከታተሉ
መለያዎን በመጠቀም የቅሬታዎን ሁኔታ በማንኛውም ጊዜ ይከታተሉ። ለተጨማሪ መረጃ ማስታወቂያዎችን ይመልከቱ።
ፈጣን የቅጣት ማጣቀሻ
ተለመዱ የአስተዳደር መቀስቀሻዎች (ሙሉ ዝርዝር በቅጣት ገጽ ያረጋግጡ)።
ቆሻሻ መጣል (ሲጋራ፣ ወረቀት፣ ፍራፍሬ ወዘተ)
የቤት ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ መጣል
ከተሽከርካሪ ላይ ቆሻሻ መጣል
ከመጸዳጃ ቤት ውጭ ሽንት መሽናት
የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም
ከቤት 5 ሜትር ራዲየስ ውጭ ያለውን አካባቢ አለማጽዳት
የግንባታ ቆሻሻ መጣል
የሞተ እንስሳን ባልተፈቀደ ቦታ መጣል
ወንዝን መበከል (የፍሳሽ ቆሻሻ ማፍሰስ)
ቆሻሻ መጣል (ሲጋራ፣ ወረቀት፣ ፍራፍሬ ወዘተ)
የቤት ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ መጣል
ከተሽከርካሪ ላይ ቆሻሻ መጣል
ከመጸዳጃ ቤት ውጭ ሽንት መሽናት
የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም
ከቤት 5 ሜትር ራዲየስ ውጭ ያለውን አካባቢ አለማጽዳት
የግንባታ ቆሻሻ መጣል
የሞተ እንስሳን ባልተፈቀደ ቦታ መጣል
ወንዝን መበከል (የፍሳሽ ቆሻሻ ማፍሰስ)
ቆሻሻ መጣል (ሲጋራ፣ ወረቀት፣ ፍራፍሬ ወዘተ)
የቤት ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ መጣል
ከተሽከርካሪ ላይ ቆሻሻ መጣል
ከመጸዳጃ ቤት ውጭ ሽንት መሽናት
የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም
ከቤት 5 ሜትር ራዲየስ ውጭ ያለውን አካባቢ አለማጽዳት
የግንባታ ቆሻሻ መጣል
የሞተ እንስሳን ባልተፈቀደ ቦታ መጣል
ወንዝን መበከል (የፍሳሽ ቆሻሻ ማፍሰስ)
ቆሻሻ መጣል (ሲጋራ፣ ወረቀት፣ ፍራፍሬ ወዘተ)
የቤት ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ መጣል
ከተሽከርካሪ ላይ ቆሻሻ መጣል
ከመጸዳጃ ቤት ውጭ ሽንት መሽናት
የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም
ከቤት 5 ሜትር ራዲየስ ውጭ ያለውን አካባቢ አለማጽዳት
የግንባታ ቆሻሻ መጣል
የሞተ እንስሳን ባልተፈቀደ ቦታ መጣል
ወንዝን መበከል (የፍሳሽ ቆሻሻ ማፍሰስ)
በመጫን ላይ…

