
የወንዝ ዳርቻ ልማትና ጥበቃ
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ቁጥር 180/2016 — የተከለከሉ ዞኖችና ተግባራት።
የወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል — ደንብ ቁጥር 180/2016
የወንዝ ዳርቻ ጥበቃ ክልል
የወንዝ ዳርቻዎች ከወንዙ ጠርዝ ጀምሮ በሁለቱም አቅጣጫ ቢያንስ 30 ሜትር የጥበቃ ክልል ናቸው። በዚህ ክልል ውስጥ የሚከተሉት ተግባራት የተከለከሉ ናቸው፦
- ማንኛውም ዓይነት ግንባታ ማካሄድ
- የንግድ ወይም ሌሎች አገልግሎቶችን መስጠት
- የወንዙን ተፈጥሯዊ ፍሰት የሚቀይሩ ተግባራት
በወንዞችና በወንዝ ዳርቻዎች የተከለከሉ ተግባራት
| ዝርዝር መግለጫ | የህግ ማጣቀሻ |
|---|---|
| ከጤና ተቋማት፣ ከጋራዦችና ከመኪና ማጠቢያዎች የኬሚካል ቆሻሻ ማፍሰስ | አንቀጽ 7(1) |
| ደረቅ ቆሻሻዎችን፣ ፕላስቲኮችንና የግንባታ ቆሻሻን ወደ ወንዝ መጣል | አንቀጽ 7(2) |
| ያልተጣራ የፍሳሽ ቆሻሻን ወይም የሽንት ቤት ፍሳሽን ወደ ወንዝ ማፍሰስ | አንቀጽ 7(3) |
| በወንዝ ዳርቻዎች ላይ ማስታወቂያ መለጠፍ | አንቀጽ 7(11) |
| በወንዝ ዳርቻ ላይ ተሽከርካሪ ማጠብ | አንቀጽ 7(12) |
| በጥበቃ ክልል ውስጥ እንስሳትን ማሰማራት | አንቀጽ 7(13) |
| ያለ ፈቃድ የፕላስቲክ ቤቶችን ወይም ሌሎች ግንባታዎችን ማካሄድ | አንቀጽ 7(14) |
ለወንዝ ብክለት የሚጣሉ አስተዳደራዊ ቅጣቶች
| የጥሰቱ ዓይነት | ለግለሰብ | ለድርጅት |
|---|---|---|
| ከጤና ተቋማት፣ ከጋራዦችና ከመኪና ማጠቢያዎች የኬሚካል ቆሻሻ ወደ ወንዝ መጣል | የለም | 400,000 ብር |
| ደረቅ ቆሻሻዎችን (ፕላስቲክ፣ ጎማ፣ የሞተ እንስሳ፣ የግንባታ ቆሻሻ ወዘተ) ወደ ወንዝ መጣል | 20,000 ብር | 100,000 ብር |
| ያልተጣራ የፍሳሽ ቆሻሻን ወይም የሽንት ቤት ፍሳሽን ወደ ወንዝ ማፍሰስ | 150,000 ብር | 300,000 ብር |
| በወንዝ ውስጥ ወይም በወንዝ ዳርቻዎች ላይ ማስታወቂያ መለጠፍ | 2,000 ብር | የለም |
| ወንዝ ዳርቻ ላይ ተሽከርካሪ ማጠብ | የለም | 400,000 ብር |
| በወንዝ ዳርቻ ጥበቃ ክልል ውስጥ እንስሳትን ማሰማራት | የለም | 30,000 ብር |
| ያለ ፍቃድ ግንባታ ማካሄድ ወይም የፕላስቲክ ቤቶችን መሥራት | የለም | 200,000 ብር |
የወንዝ ብክለትን ማሳወቅ
- ማንኛውም ሰው ብክለት ሲመለከት ለአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ማሳወቅ ይችላል
- ሪፖርቱ በአካል፣ በጽሑፍ፣ በስልክ ወይም በኢሜይል ሊቀርብ ይችላል