
ሕጎችና ደንቦች
የፌዴራል አዋጆች፣ የከተማው መስተዳድር ደንቦችና መመሪያዎች።
ለነዋሪዎችና ለንግድ ማህበረሰቡ የተዘጋጁ ሕጋዊ ማጠቃለያዎች። ሙሉ የሕግ ጽሑፎቹን ለማግኘት የፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣን ወይም የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርን የሕግ ስብስቦች ይመልከቱ።
የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ አዋጅ ቁጥር 1383/2017
ቆሻሻን ምንጭ ላይ መቀነስ፣ በዓይነት መለየትና የፕላስቲክ አጠቃቀም መመሪያዎች።
ዝርዝር ይመልከቱየወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል — ደንብ ቁጥር 180/2016
የተከለከሉ የልማት ዞኖች፣ የፍሳሽ አወጋገድና የወንዝ ብክለት ቅጣቶች።
ዝርዝር ይመልከቱየደንብ ማስከበር መመሪያ ቁጥር 3/2015
የደንብ አስከባሪዎች ተግባር፣ ኃላፊነትና ለሕዝብ የሚጠበቅ የስነ-ምግባር ደረጃ።
ዝርዝር ይመልከቱየአስተዳደራዊ ቅጣቶች ሰንጠረዥ
የቆሻሻ አያያዝና የወንዝ ብክለት ቅጣቶችን በአንድ ቦታ ይፈልጉ።
ዝርዝር ይመልከቱ
ማሳሰቢያ፦ ይህ ድረ-ገጽ ለግንዛቤ ማስጨበጫ የተዘጋጀ ማጠቃለያ ነው። ለሕጋዊ ክርክሮች ወይም ኦዲቶች ኦፊሴላዊ የሕግ ቅጂዎችን ይጠቀሙ።
አስፈላጊ ትርጓሜዎች
“አዋኪ ድርጊት” ማለት በባለቤትነት፣ በተከራይነት፣ ወይም በማናቸውም መልኩ በይዞታነት በያዘው ቦታ ወይም ቤት ውስጥ የመማር ማስተማር ሂደቱን በሚያውክ አኳኽን በትምህርት ቤት ዙሪያ እስከ 200 ሜትር መጠነ ዙሪያ ክልል ውስጥ ቁማር እንዲጫወቱበት ወይም እዲያጫውቱበት፣ የመኝታ ቤት ንግድ አገልግሎት መክፈት፣ ፊልም እና ቪዲዮ ማሳየት፣ የቀንም ሆነ የሌሊት ጭፈራ መፈጸም፣ ማንኛውንም አይነት የአልኮል መጠጥ መሸጥ እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፤
“ደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻ’’ ማለት ከመኖሪያ ቤት፣ ከንግድ፣ ከኢንዱስትሪ፣ ከጋራዥ፣ ከመንገድ ፅዳት፣ ከግንባታ፣ ከግብርና፣ ከመሬት ቁፋሮ ወይም ከጠቅላላው የሕብረተሰቡ ሥራዎች ወይም በእንስሳት ምክንያት የሚፈጠር፣ ጠጣር ወይም ከፊል ጠጣር ቆሻሻ ነው፤
“ፍሳሽ ቆሻሻ’’ ማለት ከመኖሪያ ቤት፣ ከኢንዱስትሪ፣ ከጋራዥ፣ ከማንኛውም መንግሥታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሚወጣ የልብስ፣ የምግብ እቃዎች፣ የመጠጥ ዕቃዎች እጣቢ፣አተላ፣ አምቡላ፣ የመፀዳጃ ቤት ፈሳሽ፣ የእንስሳት ማደሪያ ፍሳሽ፣ መርዛማ ንጥረ ነገር ያዘለ ወይም ያላዘለ ፍሳሽ የመሳሰሉት ነው፤